በትምህርት ሚንስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎች ብቻ ላይ ሳይሆን ትምህርት ቤቶች ላይ ጭምር ትኩረት በማድረግ መምህራኖችን በማሰልጠን እና መማሪያ መጽሐፎች ላይም ማሻሻያ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋት ስራዎች ላለፉት አመታ ቢሰሩም ጥራቱ ላይ ግን እብዛም መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው ላለፉት 3 አመታት ግን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ትምህርት ሚኒስቴር ትላልቅ ማሻሻያዎች ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ላለፉት አመታት እንደተደረገው ሪሚዲያል በመውሰድ በድጋሚ የመፈተን እድል እንዳላቸው እና ቴክኒክ እና ሞያ እንደሚማሩም አስታውሰዋል፡፡
የሚኮርጅ ሰው የትም አይደርስም የሚሉት ሃላፊው ተማሪዎች እንዳይወድቁ ሲባል ቁጥጥሩን ማላላት የለብንም ብለዋል፡፡
የትምህርት ስራ ቶሎ የሚታይ ሳይሆን ቀስ በቀስ በለውጥ የሚመጣ ነው የሚሉት የትምህርት ስራ አመራር ባለሞያው ግርማ መኮንን (ዶ/ር) ያለፉት 3 አመታት ውጤት ሲገመገም የሚያስደነግጥ ቢሆንም ወደፊት የተሻለ ነገር እንደሚመጣ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡