የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ሐሙስ 8:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
የክብር ሽኝት መርሃ ግብሩ፤ ሳሪስ አደይ አበባ አዲስ ሠፈር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ይጀምራል። ከዛም ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሽኝት እንደሚከናወን ተገልጿል።
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በኬንያ ናይሮቢ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ትናንት መስከረም 7 ቀን 2017 ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል። አስክሬናቸውም ትናንት ምሽቱን አዲስ አበባ ደርሷል፡፡