ትላንት ምሽት በሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፉት ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ምሽቱን “ የተሳካ ምሽት “ ሲሉ ገልፀውታል።
ያቀዱትን በምሽቱ የካራባኦ ድል ማሳካታቸውን የገለፁት ቴን ሀግ “ ያቀድነውን አሳክተናል ፣ ደጋፊዎቻችንንም አዝናንተናል ደስተኞች ነን “ ብለዋል።
“ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ትልቅ ነገር የማሳካት እቅድ አለን ፣ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል። “ ቴን ሀግ
በምሽቱ ጨዋታ ስለ ቡድናቸው ጎል ማግባት የተናገሩት ቴን ሀግ “ ከማርከስ ራሽፎርድ በተጨማሪ ሁሉም የቡድን አባለት ጎል የማግባት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው “ ብለዋል።
በጨዋታዎቹ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ፍንጭ የሰጡት ቴን ሀግ “ በእንያንዳንዱ ጨዋታ መጀመር የሚችሉ ከአስራ አንድ በላይ ተጫዋቾች አሉን ብለዋል።